የቶተንሀሙ የመስመር አጥቂ ሰን ክለቡን እንደሚለቅ ይፋ ያደረገው ዛሬ ነው።
ደቡብ ኮሪያዊ የቶትንሃም አምበል ከጀርመኑ ባየር ሊቨርኩሰን ነበር ከ10 ዓመታት በፊት ለእንግሊዙ ክለብ የፈረመው።
ተጫዋቹ 454 ጊዜ ተጫውቶ 173 ግቦችን ማስቆጠሩን ቢቢሲ አስነብቧል። በግሉ ወጥ በኾነ አቋም ክለቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ በተጠናቀቀው ዓመት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ከቶትንሃም ጋር አሳክቷል።
ሰን በቀጣይ ወደ የትኛው ክለብ ያመራል የሚለው ጥያቄ ግን ገና አልተመለሰም።