በሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ ግማሽ ፍጻሜ ደርሳለች።

0
59

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታን እያካሄደ ነው። እንግሊዝን ከስዊድን ያደረጉት ጨዋታም በእንግሊዝ የበላይነት ተጠናቅቋል።

ሁለቱ ቡድኖች በጨዋታው በመደበኛው ሰዓት 2ለ2 አቻ ተለያይተዋል።

ከመደበኛ የጨዋታ ክፍለጊዜ በኋላ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ግብ ለማስቆጠር ጥረት ቢደረግም ማሳካት ግን አልተቻለም።

ጨዋታውም ወደ ፍጹም ቅጣት ምት አምርቶ የእንግሊዟ ግብ ጠባቂ ሀና ሃምፕተን ሁለት የፍጹም ቅጣት ምቶችን በማዳን እንግሊዝን ታድጋለች።

በመጨረሻም እንግሊዝ ስዊድንን በፍጹም ቅጣት ምት 3ለ2 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

በሌላ ጨዋታ ዛሬ ስፔን ከስዊዘርላንድ ይጫወታሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here