ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕንገቲች በአበረታች መድኃኒት ተጠርጥራ በጊዜያዊነት ከውድድር ታግዳለች።
ኤአይዩ (AIU) በሰጠው መግለጫ በቼፕንገቲች ደም ናሙና ላይ ሃይድሮክሎሮቲያዛይድ (HCTZ) የተባለ መድኃኒት ተገኝቷል።
የ30 ዓመቷ ሩት ቼፕንገቲች እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ጥቅምት 2024 በቺካጎ ማራቶን በ2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ በመግባት የዓለም ክብረ ወሰን መስበር ችላለች።
ክብረወሰኑ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ በ2023 በበርሊን ማራቶን የተያዘ የነበረር። አትሌቷ ክብረ ወሰኑን በሁለት ደቂቃ አሻሽላው ነበር ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን