ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ቼልሲ የፊፋ የክለቦች ዓለም ዋንጫን ፍጻሜ ጨዋታ ላይ ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን በፍጹም የጨዋታ የበላይነት አሸንፎ ዋንጫውን አንስቷል። ቸልሲ ፒ ኤስ ጅን 3 ለ 0 ነው በማሸነፍ ዋንጫውን ያነሳው።
የማሸነፊያ ግቧን ኮል ፓልመር በ22ኛው እና በ30ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር አዲሱ የሰማያዊዎቹ ፈራሚ ጆአዎ ፔድሮ በ43ኛው ደቂቃ ላይ ሦስተኛውን ግብ አስቆጥሯል።
በሁለተኛው አጋማሽ ፒኤስ ጅ የግብ ክፍተቱን ለማጥበብ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካለትም።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን