የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ በማቅናት ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው፡፡

0
135

አዲስ አበባ: ሰኔ 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዋልያዎቹ ወደ አሜሪካ በሚያቀኑበት ወቅት ሙሉ ወጭው በዲሲ ዩናይትድ እንደሚሸፈን እና በጨዋታው በመካፈላቸው ብቻ የ25 ሺህ ዶላር፤ ጨዋታውን ካቨነፉ ደግሞ የ50ሺህ ዶላር ሽልማት እንደሚበረከትላቸውም ተገልጿል፡፡

ስምምነቱን በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ባህሩ ጥላሁን እና የዲሲ ዩናይትድ ባለድርሻ እዮብ ማሞ በተገኙበት መግለጫ ተሰጥቷል። ስምምነቱ ለሦስት ዓመታት እንደሚቀጥልም ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ባህሩ ጥላሁን ይህ ስምምነት ተጫዋቾች በዓለም አቀፍ መልማዮች የመታየት ዕድል እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ባለፈው ዓመት ፌዴሬሽኑ ባመቻቸው ተመሳሳይ ዕድል ሱራፌል ዳኛቸው ለአሜሪካው ክለብ ሎደን ዩናይትድ የመጫወት ዕድል ማግኘቱ ይታወሳል።

ከወንዶች በተጨማሪ ሴት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችም የሙከራ ዕድል የሚያገኙበት መድረክ መፈጠሩንም አቶ ባህሩ ተናግረዋል፡፡ ሎዛ አበራ ለዲሲ ፓወር እንድትፈርም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ዲሲ ዩናይትድ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመኾን ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን በመግለጫው ተመላክቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ነሐሴ/2017 ዓ.ም ወደ አሜሪካ ተጉዞ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ በቅርቡ ሥብሥባቸውን እንደሚሳውቁ ደግሞ የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ:- ባዘዘው መኮንን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here