ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የሚሳተፉበት የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በጅማ ከተማ እንደሚካሄድ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በ6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በ26 የስፖርት አይነቶች ከ4ሺህ 500 በላይ ስፖርተኞች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡
የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ መክዩ መሐመድ ለሁለት ሳምንት የሚቆየው ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ላይ ትኩረት ተደርጎ እነደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
ለውድድሩ በቂ ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ ውድድሩ ከሰኔ 10/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን