ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኖርዌይ ኦስሎ በተደረገው የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር የኔዋ ንብረት አሸናፊ ኾናለች።
የኔዋ የዓመቱን ምርጥ ሰዓቷን በማስመዝገብ ጭምር ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቃለች። 30 ደቂቃ 28 ነጥብ 82 ሰከንድ አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም ኾኗል።
ጫልቱ ዲዳ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። ጫልቱ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 30 ደቂቃ 33 ነጥብ 86 ሰከንድ ሲወስድባት የዓመቱ ምርጥ ሰዓቷም ኾኖ ተመዝግቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!