ማንቸስተር ሲቲ ቲጃኒ ሬይንደርስን አስፈረመ።

0
102

ባሕር ዳር : ሰኔ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ሲቲ የኤሲ ሚላኑን አማካይ ቲጃኒ ሬይንደርስን በ46 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ የመጀመሪያ ክፍያ በአምስት ዓመት ኮንትራት ማስፈረሙን አረጋግጧል።

የኔዘርላንዳዊ ተጫዋች ሬይንደርስ የፔፕ ጋርዲዮላ አራተኛው የዚህ የዝውውር መስኮት ፈራሚ ሲኾን ከዚህ ቀደም ራያን አይት ኑሪ፣ ማርከስ ቤቲኔሊ እና ራያን ቼርኪም ክለቡን ተቀላቅለዋል።

የ26 ዓመቱ ሬይንደርስ በዚህ ወር አሜሪካ ውስጥ በሚካሄደው የክለቦች ዓለም ዋንጫ ላይ እንዲሳተፍ ተፈልጎ ፊርማው እንዲፋጠን መደረጉ ነው የተገለጸው።

ክለቡ እንደ ፈረንጆቹ ሰኔ 18/2025 ከዊዳድ ኤፍ ሲ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ሬይንደርስ “ለማንቸስተር ሲቲ በመፈረሜ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብሏል። “ሲቲ በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ ቡድኖች አንዱ ነው፣ ምርጥ አሠልጣኝ፣ የዓለም ትልቅ ደረጃ ያላቸው ተጫዋቾች ያሉት ክለብ በመኾኑ ክለቡን በመቀላቀሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ ብሏል።

አማካዩ 22 ጊዜ ለኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፏል።

ባለፈው የውድድር ዘመን በሚላን 54 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 15 ግቦችን አስቆጥሯል።

የውድድር ዓመቱ የሴሪ ኤ ምርጥ አማካይ ተብሎም መመረጡ ይታወሳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here