ማንቸስተር ሲቲ የዎልቭስን የግራ መስመር ተከላካይ ሪያን አይት ኑሪን አስፈረመ፡፡

0
93

ባሕር ዳር: ሰኔ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ማንቸስተር ሲቲ ከዎልቭስ የ24 ዓመቱን የአልጀሪያዋ ግራ ተከላካይ ሪያን አይት ኑሪን በ31 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ማስፈረሙን አረጋግጧል።

አይት-ኑሪ እስከ 2030 ድረስ የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲኾን በዚህ ወር በሚካሄደው የክለቦች የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ኾኗል ነው ተብሏል።

አይት-ኑሪ በ2021 ከፈረንሳዩ ክለብ አንገርስ በ14 ነጥብ 9 ሚሊዮን ፓውንድ ዎልቭስን በቋሚነት ከመቀላቀሉ በፊት ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት አሳልፎ ነበር።

ባለፈው የውድድር ዘመን ዎልቭስ ከወራጅ ቀጣና እንዲርቅ በመርዳት በሁሉም ውድድሮች 41 ጨዋታዎችን አድርጎ አምስት ግቦችን በማስቆጠር እና ሰባት ለግብ የሚኾኑ ኳሶችን በማቀበል አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ተከላካየ በዚህ ክረምት ከዎልቭስ የሚለቀው ሁለተኛው ታዋቂ ተጫዋች ሲኾን ከዚህ ቀደም ብራዚላዊው አጥቂ ማቴዎስ ኩኒያ ማንቸስተር ዩናይትድን በ62 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ለመቀላቀል ስምምነት ላይ ደርሷል።

ማንቸስተር ሲቲ ከዚህ ቀደምም የኤሲ ሚላኑን አማካይ ቲጃኒ ሬይንድርስን በ46 ነጥብ 3 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ስምምነት ላይ ደርሷል።

የጋርዲዮላው ቡድን ሪያን ቼርኪንም ከሊዮን ለማስፈረም ጫፍ ደርሷል።

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here