ስፔን ከፈረንሳይ የኔሽንስ ሊግ ፍጻሜ ቦታን ለማግኘት ይጫወታሉ።

0
118

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ውድድር ፖርቱጋል ጀርመንን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሳለች። ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ደግሞ ፈረንሳይ እና ስፔን የፖርቱጋልን እግር ለመከተል ይፋለማሉ።

ስፔን ያለፈውን ዓመት ዋንጫ አሸናፊ ናት። ክብሯን ለማስጠበቅ በምታደርገው ጉዞ ዛሬ ከፈረንሳይ ከባድ ፈተና ይጠብቃታል። ፈረንሳይም ከዚህ በፊት የኔሽንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ችላለች።

የሁለቱ ቡድኖችን ጨዋታ በተለይ የፊት መስመር ተሰላፊዎቻቸው አኹን የሚገኙበት ምርጥ ብቃት ጨዋታው በእጅጉ እንዲጠበቅ አድርጎታል።

ኪሊያን ምባፔ፣ ኦስማን ደምበሌ፣ ዲስሪ ዱዌ እና ማርከስ ቱራምን የመሳሰሉ በየክለቦቻቸው ምርጥ ጊዜን ያሳለፉ የፊት መስመር ተሰላፊዎች የፈረንሳይ መተማመኛ ናቸው።

በተዳጊው ያማል የምትመካው ስፔንም ኒኮ ዊልያምስ፣ ፍራን ቶሬስ፣ ኦርዚያቫልን ይዛ ጨዋታውን እየጠበቀች ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here