ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፖርቱጋል በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ጀርመንን 2 ለ 1 በመርታት ወደ ፍጻሜው ማለፏን አረጋግጣለች።
በጨዋታው ክርሲቲያኖ ሮናልዶ ለሀገሩ የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል። ጀርመን በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ግብ በማስቆጠር ቀዳሚ ነበረች።
ነገር ግን የሮናልዶዋ ሀገር አከታትላ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ግቦች ጨዋታውን አሸንፋለች። ሮናልዶም የሀገሩን ሁለተኛ እና የማሸነፊያ ግብ በማስቆጠር በ40 ዓመቱ ታሪክ መሥራቱን ቀጥሏል።
ከዚህ በፊት የኔሽንስ ሊግ ዋንጫን ካነሱ ሀገራት መካከል አንዷ የኾነችው ፖርቱጋል ከፈረንሳይ እና ስፔን አሸናፊ ጋር በፍጻሜ የምትጫወት ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን