ፋሲል ከነማ ከወራጅ ቀጠና ለመራቅ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል።

0
91

ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከነማን ከወላይታ ድቻ ዛሬ 12፡00 ያገናኛል። በ38 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ከወራጅ ቀጠናው በሦስት ነጥቦች ብቻ ርቆ ነው የሚገኘው።

ከሦስት ተከታታይ አቻ ውጤቶች በኋላ ድል ለማድረግ የሚገባው ቡድኑ ከድል ከራቀ ስምንት የጨዋታ ሳምንታት አሳልፏል። በሊጉ በ14 ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቶ በመውጣት ቀዳሚ የኾነው ፋሲል ከነማ እያስመዘገ ያለው የአቻ ውጤት ወሳኝ ነጥቦችን እንዲያጣ እና ዘደረጃ ሠንጠረዡ እንዲንሸራተት እያደረጉትም ይገኛሉ።

በዛሬው ጨዋታ ከኳስ ቁጥጥር እና ከመከላከል አቅም አንጻር የተሻለ አሰላለፍ ይዞ ካልገባ ጨዋታውን ተቆጣጥሮ አሸንፎ ለመውጣት ሊቸገር እንደሚችል ባለፉት ካደረጋቸው ጨዋታዎች መገንዘብ ይቻላል። አጼዎቹ እዮብ ማቲያስን፣ አቤል እንዳለን፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል በጉዳት ሀብታሙ ተከስተ እና ማርቲን ኪዛን በቅጣት አያሰልፉም።

ወላይታ ድቻ በበኩላቸው በ42 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ከወራጅ ቀጣናው በሰባት ነጥብ ርቀት ላይ ተቀምጦ ነው ዛሬ ጨዋቻውን የሚያደርገው። ካለፉት አራት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ማስመዝገብ የቻለው ቡድኑ ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ነው ዛሬ ጨዋታውን የሚያደርገው።

ቡድኑ ካርሎስ ዳምጠው፣ ኬኔዲ ከበደን በቅጣት እና ብስራት በቀለን በጉዳት ሳያሰልፍ ጨዋታውን ያደርጋል። ሁለቱ ክለቦች እስካኹን 15 ጊዜ ተገናኝተዋል። ፋሲል ከነማ ሰባት ጊዜ ሲያሸንፍ 17 ግቦችን አስቆጥሯል። ወላይታ ድቻ አምስት ጊዜ አሸንፎ 15 ግቦችን አስቆጥሯል። ሦስት ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

በፕሪምየርሊጉ የዛሬ ሌላው ጨዋታ ስዑል ሽሬ ከሀዋሳ ከተማ 3፡30 እና መቀሌ 70 እንደርታ ከሲዳማ ቡና 9፡00 የሚያደርጉት ሌላው ጨዋታ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here