የዝውውር ጭምጭምታዎች!

0
170

ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ የፊት መስመሩን እና የመሐል ሜዳውን ለማጠናከር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።የብሬንትፎርዱ ካሜሩናዊ አጥቂ ብራያን ምቦሞ ደግሞ የክለቡ ምርጫ ኾኗል። ተጫዋቹም ዩናይትድን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው በመግለጹ ክለቡ

ተጫዋቹን የግሉ ለማድረግ ንግግር ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ መኾኑ ነው እየተነገረ ያለው። ምቦሞ በፕሪምየር ሊጉ ባሳየው ጥሩ አቋም እውቅናን እያገኘ ሲኾን ካለፉት የዩናይትድ የአጥቂዎች ግዥ ታሪኮች አንጻር እንደ ሉካኩ እና ኤዲንሰን ካቫኒ የመሳሰሉት ስኬታማ ያልኾኑም ዝውውሮች መኖራቸው ይታወቃል።

የዩናይትድ ደጋፊዎች በበኩላቸው አዲሱ አጥቂ በኦልድ ትራፎርድ የጎል ድርቀትን እንደሚፈታ ተስፋ አድርገዋል። በሌላ በኩል ኢንተር ሚላን የማንቸስተር ዩናይትድ እና የዴንማርክ አጥቂን ራስሙስ ሆይሉንድን በውሰት ለማስፈረም ተስፋ አድርጎ እየሠራ ነው የሚገኘው።

ሆይሉንድ ባለፈው የውድድር ዘመን የዩናይትድን አጥቂ ክፍል በመምራት ከተጠበቀው በላይ ጫና ገጥሞት የነበረ ሲኾን የውሰት ዝውውሩ ለወጣት ተጫዋቹ የተሻለ ዕድል ሊሰጠው ይችላል ነው የተባለው። የክለቡ ቁልፍ ተጫዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ የወደፊት እጣ ፈንታው አልታወቀም። ፈርናንዴዝ በዩናይትድ

ውስጥ የቡድኑ ሞተር በመኾን ጉልህ ሚና ሲጫወት የቆየ ሲኾን የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል-ሂላል ለእሱ ፍላጎት ማሳየቱ የመሐል ሜዳውን ሊያዳክም ይችላል ተብሏል። ዩናይትድ ባለፉት ዓመታት እንደ ፖል ፖግባ እና አንደር ሄሬራ የመሳሰሉ ወሳኝ አማካዮችን አጥቷል፤ በመኾኑም የፈርናንዴዝ መልቀቅ

ለቡድኑ ትልቅ ጉዳት ሊኾን ይችላል። በሌላ በኩል ማንቸስተር ዩናይትድ የክሪስታል ፓላሱን ፈረንሳዊ አጥቂ ዣን ፊሊፕ ማቴታን በዝውውር ከሚፈልጋቸው ዝርዝሩ ውስጥ አስገብቶታል።

ማቴታ በፕሪምየር ሊጉ ባሳየው ጠንካራ ብቃት ይታወቃል፣ ነገር ግን ዩናይትድ ከጁቬንቱስ እና ኤሲ ሚላን ጠንካራ ፉክክር ሊገጥመው ይችላል። በሌላ ዜና የ18 ዓመቱ የእንግሊዝ ተከላካይ ማይልስ ሌዊስ-ስኬሊ በአርሰናል አዲስ ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ እርምጃ አርሰናል ወጣት ተጫዎቾችን ለማሰባሰብ የሚያደርገውን ጥረት ያሳያል፣ በተለይም እንደ ቡካዮ ሳካ ያሉ ተጫዋቾች ከወጣት አካዳሚው ወጥተው ለቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች መኾናቸው ይታወቃል። ሊቨርፑል ከጀርመናዊው አማካይ ፍሎሪያን ዊርትዝ ጋር እስከ 2030 የሚቆይ ውል ቢስማማም፣

ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር የዝውውር ክፍያን በተመለከተ መስማማት አልቻለም። ሌቨርኩሰን የ130 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ክፍያን ውድቅ አድርጎ 150 ሚሊዮን ዩሮ እየጠየቀ ነው። ይህ የዝውውር ታሪክ ከሊቨርፑል ትልልቅ የዝውውር ክፍያዎች መካከል እንደ ቨርጂል ቫን ዳይክ እና አሊሰን ቤከር ያሉ

ተጫዋቾች ጋር ተመሳሳይ ይኾናል። ባርሴሎና የሊቨርፑል ኮሎምቢያዊ የክንፍ ተጫዋች ሉዊስ ዲያዝ ጋር እየተነጋገረ ይገኛል። የሳውዲ አረቢያ ክለቦችም ለተጫዋቹ ፍላጎት አላቸው። ባርሴሎና በፋይናንስ ችግሮች ውስጥ ባለበት ወቅት እንዲህ ዓይነቱን ትልቅ ዝውውር ማከናወን አስቸጋሪ ሊኾን ይችላል።

ቼልሲ የኤቨርተኑን የእንግሊዝ ማዕከላዊ ተከላካይ ጃራድ ብራንትዋይትን ለማስፈረም ፍላጎት ያሳየ ሲኾን ቶተንሃምም በዚህ ክረምት ሊወዳደረው ይችላል ነው የተባለው። ሁለቱም ክለቦች የተከላካይ መስመራቸውን ለማጠናከር ይፈልጋሉ፣ በተለይም ቼልሲ ባለፉት ዓመታት በተከላካዮች ዝውውር ላይ ከፍተኛ

ገንዘብ ሲያወጣ ቆይቷል።ቼልሲ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱን የእንግሊዝ ክንፍ ተጫዋች ጄሚ ጊተንስን ለማስፈረም እያሰበ ሲኾን ዝውውሩ ወደ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ሊጠይቀው ይችላል እየተባለ ይገኛል። ማንቸስተር ሲቲ የኤሲ ሚላን እና የኔዘርላንድን አማካይ ቲያኒ ሬይደርስን እንደ ፈረንጆቹ ሰኔ 14 በአሜሪካ

ከሚጀመረው የፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ አስቀድሞ ለማስፈረም ተቃርቧል። ኤቨርተን፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም የሰርቢያውን አጥቂ አሌክሳንደር ሚትሮቪችን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል፤ አል-ሂላል ደግሞ እሱን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። ሚትሮቪች ከዚህ በፊት ወደ ሳውዲ አረቢያ ያደረገው

ዝውውር ብዙዎችን አስገርሞ ነበር። የቀድሞው የአርሰናል እና የእንግሊዝ አማካይ ጃክ ዊልሼር የሊግ አንድ ክለብ የኾነውን ፕሊማውዝ አርጋይልን አሠልጣኝነት ለመረከብ ግንባር ቀደም እጩ ኾኗል። ዊልሼር በእግር ኳስ ሕይወቱ በጉዳት ብዙ የተሰቃየ ቢኾንም የእግር ኳስ ዕውቀቱ እና ልምዱ በአሠልጣኝነት

ሥራው ውጤታማ ሊያደርገው ይችላል ነው እየተባለ የሚገኘው። ይህ የፕሊማውዝ ውሳኔ የአሠልጣኝነት ልምድ የሌላቸውን የቀድሞ ተጫዋቾችን ወደ አሠልጣኝነት የማምጣት ፍላጎትን ያጭራል ነው እየተባለ ያለው።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here