ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) እንግሊዛዊ ተጫዋች አርኖልድ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል መስማማቱ ይታወሳል። ሪያል ማድሪድ አሌክሳንደር አርኖልድን በዓለም የክለቦች ዋንጫ ለማጫወት እና ሊቨርፑል ቀድሞ እንዲለቀው የ10 ሚሊዮን ዩሮ ክፍያ ለሊቨርፑል ከፍሏል።
በዚህ ስምምነት መሠረት አርኖልድ ዛሬ በይፋ የማድሪድ ተጫዋች ኾኗል። አርኖልድ በነጮቹ ቤት ለቀጣይ ስድስት ዓመታት ለመቆየት ተስማምቷል።
አሌክሳንደር አርኖልድ ለቀዮቹ 352 ጨዋታዎችን አድርጎ 23 ግቦችን አስቆጥሯል። 86 ግብ የኾኑ ኳሶችንም አቀብሏል።
ከሊቨርፑል ጋር ሁለት የፕሪሚየር ሊግ፣ አንድ የቻምፒየንስ ሊግ፣ የፊፋ ክለቦች ዓለም ዋንጫ፣ የዩኤፋ ሱፐር ካፕ፣ የኤፍኤ ካፕ እና የሊግ ካፕንም አሸንፏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን