ባሕር ዳር: ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 👉 ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሰኔ 15 በአሜሪካ በሚጀመረው የክለቦች የዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ሲል የሳዑዲ ፕሮ ሊጉን ክለብ አል-ናስርን ሊለቅ እንደሚችል እየተነገረ ነው። ሮናልዶ በአልናስር አኹን ላይ ደስተኛ አለመኾኑም በሚዲያዎች እየተነሳ ነው።
👉 ማንቸስተር ዩናይትድ የወልቭሱን የፊት መስመር ተጫዋች ማቲያስ ኩኛ ለማስፈረም ተቃርቧል። ዩናይትድ ለ26 ዓመቱ ብራዚላዊ የውል ማፍረሻ 62 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል መስማማቱን ተከትሎ ከተጫዋቹ ጋር ንግግር እንዲያደርግ በወልቭስ በኩል ፈቃድ ተሰጥቶታል።
👉 የሳዑዲው አል-ሂላል የማንቸስተር ዩናይትዱን አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቧል። ፖርቱጋላዊው አማካይ በ72 ሰዓታት ውስጥ ውሳኔ እንዲሰጥ እንደተነገረው ተዘግቧል።
👉 ማንቸስተር ሲቲ የሊዮኑን የ21 ዓመት ፈረንሳዊ አማካይ ሪያን ቼርኪን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ገብቷል። ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ከማንቸስተር ዩናይትድ ሊቨርፑል እና ከቼልሲ ጋር ስሙ ተያይዞ ሲነሳ ቆይቷል።
👉 ኤቨርተን ከኒውካስትል ዩናይትድ ካለም ዊልሰንን ለማስፈረም ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ፉክክር ውስጥ ገብቷል። ዊልሰን የኒውካስትል ውሉን አጠናቅቋል።
👉 ቶትንሃም የባየር ሙኒኩን ጀርመናዊ የመስመር ተጫዋች ሊሮይ ሳኔን የማስፈረም ዕድል እንደቀረበለት ተነግሯል። ሳኔ የሙኒክ ውሉን አጠናቅቋል።
👉 አርሰናል የቪክቶር ግዮኬሬስን ወኪል ሊዝበን ውስጥ እንዳነጋገረ እና ስዊድናዊውን ተጫዋች ለማስፈረም የ58 ነጥብ 7 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ እንዳቀረበ ተዘግቧል።
👉 ማንቸስተር ዩናይትድ የኢፕስዊች ታውንን እንግሊዛዊ አጥቂ ሊያም ዲላፕን ለማስፈረም የስምምነት ማዕቀፍ እንዳዘጋጀ እና አኹን ላይ ተጫዋቹ ቀጣይ የዝውውር ውሳኔውን እንዲያሳውቅ እየጠበቀ መኾኑ ተገልጿል። ዘቴሌግራፍ፣ ስካይ ስፖርት፣ ዘ ሰን እና ዴይሊ ሜይል የመረጃ ምንጮቻችን ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን