በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋርቷል።

0
81

ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ31ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዛሬ ሲካሄድ ፋሲል ከነማ ከሀዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋርቷል። ጨዋታውም 1ለ1 በኾነ ውጤት ተጠናቅቋል። የሀዋሳ ከተማ ግብን ዓሊ ሱሌይማን ሲያስቆጥር የፋሲል ከነማን የአቻነት ግብ ባለቀ ሰዓት ጌታነህ ከበደ አስቆጥሯል።

ሌላው ጨዋታ በስዑል ሽሬ እና በመቀለ 70 እንደርታ መካከል የተካሄደው ሲኾን መቀለ 70 እንደርታ 2ለ1 በኾነ ውጤት አሸንፏል። ፕሪሚየር ሊጉን ኢትዮጵያ መድን በ60 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና በ54 ሁለተኛ እና ባሕር ዳር ከተማ በ48 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here