ባሕር ዳር: ጥር 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሳዑዲው አል ናስር የ25 ዓመቱን የቶትንሃም የቀኝ መስመር ተከላካይን ኤመርሰን ሮያል ለማስፈረም 20 ሚሊዮን ፓውንድ ማቅረባቸውን ቴሌግራፍ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡
ቪክቶር ኦሲሜን ናፖሊን ለመልቀቅ ዝግጁ መኾኑን ፍንጭ ሰጥቷል። ቼልሲ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ የ25 ዓመቱን ናይጄሪያዊ የፊት አጥቂ ለማስፈረም 100 ሚሊዮን ፓውንድ አቅርበዋል፡፡
የ76 ዓመቱ የክሪስታል ፓላሱ አለቃ ሮይ ሆጅሰን የቡድናቸው ውጤት ካልተሻሻለ ሊባረሩ እንደሚችሉ ቡድናቸው ማስጠንቀቂያ እንደሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡
ሼፊልድ ዩናይትድ የ28 ዓመቱን ክሮሺያዊ የአትሌቲኮ ማድሪዱን ግብ ጠባቂ ኢቮ ግሪቢክ ለማስፈረም ጫፍ መድረሱን አስታውቋል፡፡
ባየር ሙኒክ ኪይራን ትሪፒየርን ከኒውካስትል ዩናይትድ ላይ በ15 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉን አስታውቋል፡፡
ዌስትሃም እንግሊዛዊውን አማካኝ ካልቪን ፊሊፕስን ከማንቸስተር ሲቲ ላይ በውሰት ውል ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ፡፡
የ28 ዓመቱ ፊሊፕስ እንደ አውሮፓውያን ዘመን በሰኔ 2022 ነበር በ45 ሚሊዮን ፓውንድ ማንቸስተር ሲቲን የተቀላቀለው፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!