በ9ኛው በመላ አማራ ጨዋታዎች የቼዝ እና የዳርት ውድድሮች ተጠናቀቁ።

0
93

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በቼዝ ውድድር ስድስት ዞኖች ተሳትፈዋል። ማዕከላዊ ጎንደር በሦስት ወርቅ፣ አራት ብር እና አንድ ነሐስ ሜዳሊያዎች አንደኛ ኾኖ ጨርሷል።

ደቡብ ወሎ ሦስት ወርቅ፣ ሁለት ብር እና ሁለት ነሐስ ሁለተኛ ሲኾን ደሴ ከተማ ሦስት ወርቅ እና አራት ነሐስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የዳርት ውድድሩም ዛሬ ተጠናቋል። በዳርት ስፖርት ዘጠኝ ዞኖች ተሳትፈዋል። ሰሜን ሸዋ ሦስት ወርቅ፣ ሁለት ብር እና ሁለት ነሐስ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ አጠቃላይ አሸናፊ ኾኗል።

ደብረ ብርሃን ከተማ በሦስት ወርቅ፣ አንድ ብር እና ሁለት ነሐስ ሁለተኛ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በአንድ ወርቅ፣ አራት ብር እና ሁለት ነሐስ ሦስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here