የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ለማሳካት አምስት ቡድኖች ተፋጥጠዋል።

0
88

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በቀጣይ ሳምንት ይጠናቀቃል። እስከ ሊጉ 37ኛ ሳምንት ድረስ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፋ ቡድኖች ሙሉ በሙሉ አለመለየታቸው የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ተጠባቂ እንዲኾኑ አድርጓል። በቀጣዩ የውድድር ዓመት እንግሊዝ በሻምፒዮንስ ሊጉ በስድስት ቡድኖች ትወከላለች። ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል እና አርሰናል የሻምፒዮንስ ሊጉ ቦታቸው ተረጋግጧል።

ከዩሮፓ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚዎቹ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶትንሃም መካከል የዋንጫ ባለቤቱ በቀጣይ በሻምፒዮንስ ሊጉ መሳተፉም ሀቅ ነው። ቀሪ ሦስት ቦታዎችን ለማግኘት ደግሞ አምስት ቡድኖች ተፋጥጠዋል። ኒውካስትል ዩናይትድ፣ ቼልሲ እና አስቶን ቪላ እኩል 66 ነጥብ ይዘው በግብ ክፍያ ተለያይተው በደረጃ ሰንጠረዡ ከሦስተኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ማንቸስተር ሲቲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት በተመሳሳይ 65 ነጥብ ስድስተኛ እና ሰባተኛ ናቸው። ሲቲ አንድ ቀሪ ጨዋታ ይቀረዋል። ከእነዚህ አምስት ቡድኖች መካከል ሦስቱ በቀጣይ ጨዋታዎች በሚያስመዘግቡት ውጤት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳተፎ ቦታን ያገኛሉ። በቢቢሲ መረጃ መሠረት ከበርንማውዝ እና ፉልሃም ጋር ጨዋታዎችን የሚያደርገው የጋርዲዮላው ቡድን የተሻለ ዕድልም አለው።

ኒውካስትል ዩናይትድ በሜዳው ከኤቨርተን፣ ቼልሲ ከሌላኛው የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታ ፈላጊ ኖቲንግሃም ፎረስት የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ከፍተኛ ተኩረትን አግኝተዋል። አስቶን ቪላ ደግሞ በመጨረሻ ቀን ጨዋታ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ይጫወታል። ማንቸስተር ሲቲ፣ ኒውካስትል እና ቼልሲ የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው ይወስናሉ። የመጨረሻ ጨዋታቸውን ማሸነፍ ከቻሉ የሌሎች ቡድኖችን ውጤት ሳይጠብቁ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፏቸውን ያረጋግጣሉ። ሲቲ ቀሪ ጨዋታውንም የሚያሸንፍ ከኾነ ማለት ነው።

በአስማማው አማረ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here