በመላው አማራ ስፖርታዊ ጨዋታዎች የክብደት ማንሳት ውድድር ደሴ ከተማ አጠቃላይ አሸናፊ ኾኗል።

0
103

ደሴ: ግንቦት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 9ኛው የመላው አማራ ስፖርታዊ ጨዋታዎች የክብደት ማንሳት ውድድር በደሴ ከተማ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። አራት ዞኖችን ያሳተፈው የክብደት ማንሳት ውድድር ላለፉት አራት ቀናት ሲያካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል።

ደሴ ከተማ ውድድሩን አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 3 ወርቅ እና 2 ብር ሜዳሊያዎችን አሸንፏል።

ደቡብ ጎንደር እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር 1 ወርቅ 1 ብር እና 1 ነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል። ደቡብ ወሎ አንድ ብር እና አንድ ነሐስ በማግኘት ውድድሩን አጠናቅቋል።

ዘጋቢ: ኃይሉ አዳነ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here