ፋሲል ከነማ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

0
114

ባሕር ዳር: ግንቦት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፋሲል ከነማ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ጠዋት 3፡30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ፋሲል ከነማ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች አቻ ከተለያየ በኋላ ይህን ጨዋታ ሦስት ነጥብ ይዞ ለመውጣት ነው የሚጫወተው።

በ35 ነጥብ በ10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ አፄዎቹ ። አሠልጣኝ ውበቱ አባተም ይህን የቡድኑን ችግር ቀርፈው ዛሬ ሦስት ነጥብ ይዘው እንደሚወጡ ነው የሚጠበቀው። በሌላ በኩል ተጋጣሚው ኢትዮጵያ መድን በ54 ነጥብ ሊጉን እየመራ የሚገኝ ነው። ሳምንት ከባሕር ዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ሽንፈት ማስተናገዱ ይታወሳል።

በዚህ ጨዋታ በፋሲል ከነማ በኩል አቤል እንዳለ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል እና በረከት ግዛው በጉዳት ምክኒያት በዛሬው ጨዋታ አይሰለፉም። በኢትዮጵያ መድን በኩልም ሚልዮን ሰለሞን ለጨዋታው ብቁ አይደለም። ሁለቱ ቡድኖች ቀደም ሲል በሊጉ ስድስት ጊዜ ተገናኝተዋል። ፋሲል ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ መድን አንድ ጊዜ አሸንፏል። ቀሪዎቹ አቻ የተጠናቀቁ ጨዋታዎች ናቸው።

ሌሎች ጨዋታዎችም ዛሬ ሲደረጉ ድሬዳዋ ከተማ ከመቀለ 70 እንደርታ 9፡00ሰዓት ላይ፣ ሀድያ ሆሳዕና ከውልዋሎ 12፡00 ይጫዎታሉ። ሊጉን ኢትዮጵያ መድን በ54 ነጥብ ሲመራ፤ ኢትዮጵያ ቡና በ48 ሁለተኛ፣ ባሕርዳር ከተማ አንድ ጨዋታ እየቀረው በ46 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here