ቀኑ ተቀይሮ የነበረው የባሕርዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ መድን ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል።

0
117

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕርዳር ከተማ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ከሳምንቱ ትኩረት ካገኙ ጨዋታዎች ቀዳሚውን ሥፍራ ይዟል። ጨዋታው በዋንጫ ፉክክሩ ትልቅ ትርጉም አለው። በ54 ነጥብ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን በሰባት ተከታታይ ድሎች መሪነቱን አጠናክሮ ለመቀጠል ይጫወታል።

ባሕርዳር ከተማ በሊጉ 43 ነጥብ በመሠብሠብ በ3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ይህን ጨዋታ ማሸነፍ በዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ እንዲቆይ ያደርገዋል። ጥሩ የአጥቂ ሥፍራ ተጫዋቾች ያሉት መድን ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች 13 ግቦች አስቆጥሯል። ኢትዮጵያ መድን የተከላካይ ክፍሉም ጠንካራ ነው።

የጣና ሞገዶቹም በፈጣን አጥቂዎች የሚመራ ጠንካራ የፊት መስመር ያለው ቡድን ነው። እንደ መድን ሁሉ የተከላካይ ክፍላቸውም ጠንካራ ነው። ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን በሊጉ አምስት ጊዜ ተገናኝተዋል። ኢትዮጵያ መድን ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ የጣና ሞገዶቹ አንድ ጊዜ አሸንፈዋል። ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቁት። በእነዚህ ጨዋታዎች 15 ግቦች ተቆጥረዋል። ኢትዮጵያ መድን ስምንት ግቦችን ሲያስቆጥር ባሕርዳር ከተማ ሰባት ግቦችን አስቆጥረዋል። ከኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ሸር ካምፓኒ የተገኘው መረጃ እንደሙያመላክተው ጨዋታውም ቀን 10፡00 ይካሄዳል።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here