ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ለፍጻሜ ጨዋታው ይደርሱ ይኾን?
ማንቸስተር ዩናይትድ ከአትሌቲክ ክለብ ጋር ይገናኛል። ዩናይትዶች ወደ ባለሜዳው አትሌቲክ ክለብ ተጉዘው 3 ለ 0 በመጀመሪያው ዙር መርታታቸው ነገሩን ቀለል አድርጎላቸዋል።
አትሌቲክ ክለብም ቢኾን በዚህ የውድድር ዓመት በዩሮፓ ሊግ ብዙ የተሳኩ ጫናዎችን በመፍጠር ቀዳሚ ሲኾን ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ጨዋታውም ምሽት 4፡00 ላይ ይጠበቃል።
ሌላው የአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ መለያ የሚካሄደው በተመሳሳይ ምሽት 4፡00 ላይ በቶተንሃም እና የቦዶ/ግሊምት መካከል በሚደረገው ጨዋታ ነው።
በዚህ ጨዋታም ቶተንሃም በመጀመሪያው ዙር በሜዳው ተጫውቶ ቦዶ/ግሊምትን 3 ለ 1 በመርታቱ የተሻለ የማለፍ ዕድል ይዟል።
ቶተንሃም የሁለት ጎል ልዩነት ይዞ ወደ ኖርዌይ የሚያደርገው የዛሬ ጉዞ ምን ውጤት እንደሚያመጣ የሚጠበቅ ሲኾን ቦዶ/ግሊምት በሜዳው ባለው ጠንካራ አቋም ተዓምር ሊፈጥር እንደሚችልም ይገመታል።
ዘጋቢ:- ምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን