በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የጊዜ እና የሜዳ ለውጥ ተደርጓል፡፡

0
116

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቀሪ አራት ጨዋታዎችን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለማካሄድ ቀደም ሲል መርሐ ግብር መውጣቱ ይታወሳል፡፡

ይሁንና በሀዋሳ ከተማ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የመጫወቻ ሜዳ እና የሰዓት ለውጥ ለማድረግ መገደዱን የሊጉ የውድድር እና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ቀሪ የ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሎጊታ በሚገኘው በሀዋሳ ሰው ሠራሽ ሜዳ የሚደረጉ መኾናቸውን ኮሚቴው አብራርቷል፡፡ ዛሬ ወላይታ ድቻ ከአርባ ምንጭ ከተማ ቀን 9 ሰዓት ሎጊታ በሚገኘው በሀዋሳ ሰው ሠራሽ ሜዳ ይጫወታሉ፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ሊካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ መድን እና ባሕር ዳር ከተማ ጨዋታን በተመለከተ የውድድር እና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴው የሚኖረውን መረጃ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ከኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የውድድር እና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴው ነገ ሐሙስ ድሬዳዋ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ቀን 7:00 ፣ ሲዳማ ቡና ከመቻል 10:00 ይጫወታሉ ብሏል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here