የኢንተር ሚላን እና የባርሴሎና የሻምፒየንስ ሊጉ ትንቅንቅ!

0
148

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ እግር ኳስ ከፍተኛ ስም ካላቸው ክለቦች መካከል ኢንተር ሚላን እና ባርሴሎና ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ክለቦች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ተገናኝተዋል።

በመጀመሪያው ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ 3ለ3 በኾነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። የመልሱ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል። በኢንተር ሚላን ሜዳ ጁሴፔ ሜዛ የሚደረገው ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረት ስቧል።

በባርሴሎና ሜዳ በአቻ ውጤት የተጠናቀቀው ጨዋታ የዛሬውን ጨዋታ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።

ባርሴሎና በጣሊያን ምድር ባደረጋቸው 24 የሜዳ ውጭ ጨዋታዎች አምስት ጊዜ ብቻ ነው ማሸነፍ የቻለው።

ኢንተርሚላን ባለፉት በሜዳው ባደረጋቸው 15 የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም። 12 ጊዜ አሸንፏል፣ 3 ጊዜ ደግሞ አቻ ነው የተለያየው። በአውሮፓ ግማሽ ፍጻሜ በሜዳው ካደረጋቸው ያለፉት 11 ጨዋታዎች ዘጠኙን ማሸነፉን ቢቢሲ አስነብቧል።

ኢንተርሚላን በሜዳው ያለውን ጠንካራ ክብረ ወሰን አስጠብቆ ለፍጻሜ ይበቃል ወይስ ባርሴሎና በጣሊያን ምድር ላይ ያለውን ደካማ ክብረ ወሰን ሰብሮ ለፍጻሜ ይደርሳል? የሚለው ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- ምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here