በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
112

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ሲካሄዱ ፋሲል ከነማ ከስሑል ሽረ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። በማራኪ የጨዋታ ስልት እና በጥሩ አቋም የሚታወቁት አጼዎቹ ባለፉት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ርቋቸው ታይተዋል።

በ34 ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት አጼዎቹ ከተከታታይ ሁለት ጨዋታ ሽንፈት እና ከአንድ ጨዋታ አቻ ውጤት በኋላ የአሸናፊነትን መንፈስ ለማምጣት ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቡድኑ ከመሪዎቹ ተርታ የነበረውን ፉክክር ተንሸራትቷል።
በተለይም በማጥቃት ረገድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ከውልዋሎ አዲግራት ጋር በነበረው ጨዋታ የነበረውን ሁኔታ መመለስ አልቻለም። ለማሳያም ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻሉት አንድ ግብ ብቻ ነው። በአንጻሩ ሦስት ጊዜ መረባቸው ተደፍሯል።

በዚህ ጨዋታ ቡድኑ ይህን ሁኔታ ለመቀየር ያለበትን ክፍተት ሞልቶ ወደ ሜዳ ይገባል ተብሎም ይጠበቃል። ስሑል ሽረ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ተከታታይ የአቻ ውጤት ማስመዝገቡ ለዛሬው ጨዋታ ጥሩ ስንቅ ይኾነዋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በ19 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ በወራጅ ቀጣናው የሚገኘው ስሑል ሽረ ለአጼዎቹ ከባድ ተፎካካሪ እንደሚኾን ይጠበቃል።

በአጼዎቹ በኩል እዮብ ማቲያስ እና ሀብታሙ ተከስተ በጨዋታው እንደማይሰለፉ ነው የተገለጸው።በስሑል ሽረ በኩል ደግሞ ኬቨን አርጉዲ እና ነፃነት ገብረመድኅን በጨዋታው አይሳተፉም ተብሏል። ጨዋታውም ምሽት 12:00 ላይ ይካሄዳል።

ዛሬ ሌሎች ሁለት ጨዋታዎች ሲካሄዱ ጠዋት 3፡30 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቀን 9:00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here