ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ2011/12 የዩሮፓ ሊግ 16ቱ የመጨረሻ ዙር ጨዋታዎች ከተገናኙ በኋላ አትሌቲኾ ቢልባኦ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ መድረክ ለግማሽ ፍጻሜ ዛሬ ምሽት ይገናኛሉ። በወቅቱ በማርሴሎ ቢዬልሳ ስር የነበረው አትሌቲኮ ማንቸስተር ዩናይትድን በደርሶ መልስ አሸንፎ ነበር።
ማንቸስተር ዩናይትድ በአትሌቲኮ ቢልባኦ በአውሮፓ ውድድሮች ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሦስቱን ተሸንፏል። ብቸኛ ድሉ በ1957 የውድድር ዓመት የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ሁለተኛ ጨዋታ ላይ በኦልድ ትራፎርድ 3ለ0 ያገኘው ድል ሲኾን ይህም በድምር ውጤት 6ለ5 ለግማሽ ፍጻሜ አድርሶታል።
አትሌቲኮ ቢልባኦ በአውሮፓ ውድድሮች ለሦስተኛ ጊዜ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰ ሲኾን ቀደም ባሉት ሁለቱንም አልፏል። በ1976/77 እና በ2011/12 የውድድር ዓመት። ማንቸስተር ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዓመት የዩሮፓ ሊግ እስካኹን ያልተሸነፈ ብቸኛው ቡድን ነው። ያለ ሽንፈት ያስመዘገባቸው 12 ተከታታይ ጨዋታዎች ከሕዳር 2016 እስከ ጥቅምት 2017 ከተመዘገቡት 15 ጨዋታዎች በኋላ በአውሮፓ ውድድር ረጅሙ ነው።
አትሌቲኮ ቢልባኦ በዚህ የውድድር ዓመት በሳን ማሜስ ስድስቱንም የዩሮፓ ሊግ የሜዳ ጨዋታዎች አሸንፏል። በአንድ የውድድር ዘመን ሰባት የሜዳ ጨዋታዎችን ያሸነፈው የመጨረሻው ቡድን እ.ኤ.አ በ2016/17 አያክስ ነበር። ማንቸስተር ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዓመት 28 የዩሮፓ ሊግ ግቦችን አስቆጥሯል። ይህም በ2020/21 ካስቆጠራቸው 34 ግቦች በኋላ ከፍተኛው ሲኾን ይህም በአውሮፓ ውድድር የክለቡ ክብረ ወሰን ነው።
በዚህ የውድድር ዘመን ከማንኛውም ቡድን የበለጠ 222 ሙከራዎችን እና በተጋጣሚ ሳጥን ውስጥ 458 ንክኪዎችን አድርጓል። የአትሌቲኮ ቢልባኦ አሠልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ከ2018/19 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ከባርሴሎና ጋር እና ከሊቨርፑል ጋር ከተገናኙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ውድድር ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ይመራሉ።
የማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም በስምንት የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ሳይሸነፉ ቆይተዋል። ይህም ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን የመጀመሪያ 11 ጨዋታዎች ያለ ሽንፈት ጉዞ በኋላ በአውሮፓ ውድድር ረጅሙ ያለመሸነፍ ሪከርድ ነው። ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ31 የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች 29 ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል ይህም ሪከርድ ነው።
የአትሌቲኮ ቢልባኦ ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ በዚህ የውድድር ዓመት በሜዳው ባደረጋቸው ስድስት የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች አምስት ግቦች ላይ ተሳትፏል። ጨዋታውም ምሽት 4፡00 ይካሄዳል። በተመሳሳይ ቶተንሃም ሆትስፐር እና የኖርዌይ ክለብ ቦዶ/ግሊምት ይጫወታሉ። ቶተንሃም ሆትስፐር እና የኖርዌይ ክለብ ቦዶ /ግሊምት ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ውድድር ይገናኛሉ። ቶተንሃም ሆትስፐር ከዚህ ቀደም ከኖርዌይ ቡድኖች ጋር ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሁሉ አሸንፏል።
ቦዶ/ግሊምት ደግሞ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ሦስት የአውሮፓ ጨዋታዎች ተሸንፏል። ይህ ለቶተንሃም ዘጠነኛው የአውሮፓ መድረክ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ሲኾን ከ2018/19 የቻምፒዮንስ ሊግ በኋላ የመጀመሪያው ነው። በሌላ በኩል ቦዶ/ግሊምት በአውሮፓ እግር ኳስ ታሪክ ከየትኛውም ዋና ውድድር ግማሽ ፍጻሜ የደረሰ የመጀመሪያው የኖርዌይ ቡድን ነው።
ከ1998/99 የዩክሬኑ ዲናሞ ኪየቭ ከደረሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጨረሻዎቹ አራት ውስጥ ይወከላል። ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው ያለፉትን 19 የአውሮፓ ጨዋታዎች ሳይሸነፍ አጠናቋል። በሌላ በኩል ቦዶ/ግሊምት ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው 10 የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ብቻ አሸንፏል።
በዚህ የውድድር ዓመት ቦዶ/ግሊምት 296 ሙከራዎችን ያደረገ ሲኾን ይህም ከ2017/18 በኋላ ከፍተኛው ነው። ቶተንሃም በዚህ የውድድር ዓመት በዩሮፓ ሊግ 36 ጊዜ ለታዳጊ ተጨዋቾች ዕድል የሰጠ ሲኾን ይህም በእንግሊዝ ክለቦች ከፍተኛው ነው። ዶሚኒክ ሶላንኬ በዚህ የውድድር ዓመት ለቶተንሃም ሆትስፐር በዩሮፓ ሊግ ሰባት ግቦችን በማስቆጠር እና በማቀበል ቀዳሚ ነው።
የቦዶ/ግሊምት አሠልጣኝ ኬቲል ክኑትሰን በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የደረሱ ሁለተኛው የኖርዌይ አሠልጣኝ ናቸው። የምሽቱ 4፡00 ጨዋታም የተለያዩ ታሪኮች እንደሚጻፉበትም ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን