ባሕር ዳር: ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሚያዝያ 18/ 2017 ዓ.ም በቻይናዋ ዢያመን ከተማ ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዝግጅቱ ተጠናቅቋል።
ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ሞንዶ ዱፕላንቲስ፣ ግራንት ሆሎዌይ፣ ፌዝ ኪፕዬጎን፣ ያሮስላቫ ማሁቺክ በኤግሬት ስታዲየም በሚካሄደው ውድድር ከሚጠበቁት አትሌቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
በዚህ ውድድር አስር የዓለም ሪከርድ ባለቤቶች እና 23 የቅርብ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋዬ የምትሳተፍ ሲኾን ኬኒያን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት እውቅ አትሌቶች ከበድ ያለ ፉክክር እንደሚጠብቃት ከዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ድረገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ሌላው ስዊድናዊው የፖል ቮልት ኮከብ ሞንዶ ዱፕላንቲስ ሲኾን ባለፈው ዓመት በዚሁ ስታዲየም ስምንተኛውን የዓለም ሪከርድ ማስመዝገቡ ይታወሳል።
በሴቶች ከፍተኛ ዝላይ የዩክሬኗ ያሮስላቫ ማሁቺክ፣ የአውስትራሊያዋ ኒኮላ ኦሊስላገርስ እና ኤሌኖር ፓተርሰን ከፍተኛ ፉክክር ይጠበቃል።
እንዲሁም በአምስት ሴቶች ከ70 ሜትር በላይ ርቀት የተወረወረበት የሴቶች ዲስከስ ውርወራ ውድድር የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗን ቫላሪ አልማንን ጨምሮ በርካታ ኮከቦች ይሳተፉበታል።
በአጠቃላይ በዢያመን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ አስደናቂ ፉክክሮችን እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን