ሙሐመድ ሳላህ በሊቨርፑል ክለብ ዶክተሮች መርሲሳይድ ውስጥ ታይቶ እንዲታከም አሠልጣኝ የርገን ክሎፕ ጠየቁ፡፡

0
345

ባሕር ዳር: ጥር 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሊቨርፑል እግር ኳስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕ ሙሐመድ ሳላህ በጨዋታ ወቅት ጉዳት ከደረሰበት በኋላ በሊቨርፑል ክለብ ዶክተሮች መርሲሳይድ ውስጥ ታይቶ እንዲታከም ጠይቀዋል፡፡

ሳላህ ኮትዲቯር ውስጥ የህክምና ምርመራ አድርጓል፤ የህክምናው ውጤቱም የ31 ዓመቱ ሳላህ የኋላ ጡንቻው ችግር እንዳለበትም አረጋግጧል።

ስለኾነም የሊቨርፑል እግር ኳስ አሠልጣኝ የርገን ክሎፕ “ሳላህ በሊቨርፑል ክለብ ዶክተሮች እንዲታከም ወደ መርሲሳይድ እንዲመጣልን እጠይቃለሁ” ብለዋል፡፡

የፊት መስመር አጥቂው ሳላህ ሰሞኑን ከግብጽ ጋዜጦች መቼ ነው ወደ ግብጽ አምርተህ የምትታከመው? ” ብለው ሲጠይቁት እሱ “ወደ ሊቨርፑል አቅንቼ መታከም እፈልጋለሁ” ማለቱን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡

የግብጽ እግር ኳስ ማኀበር በበኩሉ “ሙሐመድ ሳላህ ሀገሩ ከኬፕ ቬርዴ ጋር ዛሬ የምታደርገውን ጨዋታ ከተመለከተ በኋላ ወደ እንግሊዝ ተመልሶ ህክምናውን እንዲያደርግ ተወስኗል” ብሏል።

ስለኾነም በገጠመው ጉዳት ተጫዋቹ በአፍሪካ ዋንጫ ለሀገሩ በሁለት ጨዋታዎች አይሰለፍም፡፡”ከህመሙ ካገገመና ግብጽ ወደ ቀጣዩ ዙር ካለፈች ግን ሳላህ ወደ ኮትዲቯር ተመልሶ ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ተስፋ እናደርጋለን” ብሏል፡፡ እናም ሞሐመድ ሳላህ ለህክምና ወደ እንግሊዝ መሄዱ እርግጥ መኾኑን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here