ሚያዚያ: 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና እና ፒኤስጂ ቢሸነፉም በድምር ውጤት አሸንፈው ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።
ባርሴሎና ከቦርስያ ዶርትመንድ ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 1 በኾነ ውጤት ተሸንፈዋል።
የቦርስያ ዶርትመንድን የማሸነፊያ ግቦች ሴርሁ ጉራሲ 3 ሲያስቆጥር ለባርሴሎና ቤንሴባኒ በራስ መረብ ላይ አሳርፏል።
አስቶን ቪላ ከፒኤስጂ ያደረገውን የመልስ ጨዋታ 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል።
የአስቶን ቪላን የማሸነፊያ ግቦች ቴሌማንስ ፣ ማክ ጊን እና ኮንሳ ሲያስቆጥሩ ለፒኤስጂ ሀኪሚ እና ሜንዴዝ አስቆጥረዋል።
ባርሴሎና ዶርትመንድን በድምር ውጤት 5 ለ 3 እንዲሁም ፒኤስጂ አስቶን ቪላን 5 ለ 4 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።
የዶርትመንዱ የፊት መስመር አጥቂ ሴርሁ ጉራሲ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሻምፒየንስ ሊጉ 17 የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።
ሴርሁ ጉራሲ በአንድ የሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ዓመት በርካታ የግብ ተሳትፎ በማድረግ የመሐመድ ሳላህን ሪከርድ መስበር ችሏል።
በታዘብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!