ባሕር ዳር፡ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ24ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
መቻልን ከመቀሌ 70 እንደርታ ያገናኘው ጨዋታ በመቻል 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
የመቻልን የማሸነፊያ ግብ ሽመልስ በቀለ አስቆጥሯል። የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ መቻል በ32 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ተቀምጧል።
አዳማ ከተማን ከወላይታ ዲቻ ጋር ያገናኘው ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል። በሀዲያ ሆሳዕና እና ድሬዳዋ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ ደግሞ 1ለ1 በኾነ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።
ለሀዲያ ሆሳዕና ተመስገን ብርሃኑ ሲያስቆጥር ለድሬዳዋ ከተማ ደግሞ አቤል አሰበ አስቆጥሯል።
የፕሪምዬር ሊጉን የደረጃ ሠንጠረዥ ኢትዮጵያ መድን በ45 ነጥብ ሲመራ ወላይታ ዲቺ በ37 ነጥብ ሁለተኛ ነው።
ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ በ36 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን