ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መካሄድ ይጀምራሉ። ከነዚህም መካከል የእንግሊዙ አርሰናል በሜዳው የስፔኑን ሪያል ማድሪድን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።
ሁለቱ ክለቦች እስካሁን በአውሮፓ የውድድር መድረክ አራት ጊዜ ተገናኝተዋል። አርሰናል አንድ ሪያል ማድሪድ አንድ ጊዜ ሲያሸንፉ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
የምሽቱ ጨዋታ አርሰናል ለመጀመሪያ ጊዜ የቻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እና ሪያል ማድሪድ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ ቻምፒየን ለመኾን መንገዳቸውን የሚያመቻቹበት ይኾናል።
በየሀገሮቻቸው የሊግ ደረጃ ሰንጠረዥ አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሊቨርፑል በ11 ነጥብ ተበልጦ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሪያል ማድሪድ ደግሞ በስፔን ላሊጋ ከባርሴሎና በአራት ነጥብ ዝቅ ብሎ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የሁለቱ ክለቦችን ጨዋታ ምሽት 4:00 ሰዓት ጀምሮ በአሚኮ የራዲዮ ጣቢያዎች በቀጥታ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።
ዛሬ ምሽት በሚካሄደው ሌላኛው የቻምፒየንስ ሊጉ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ የጀርመኑ ባየር ሙኒክ የጣሊያኑን ኢንተር ሚላንን ያስተናግዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!