ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ሲካሄዱ የኤቨርተን እና የአርሰናል ጨዋታ ትኩረት ስቧል።
ኤቨርተን በዚህ የውድድር ዓመት በአንፃራዊነት አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፈ ነው። ነገር ግን የቀድሞ አሰልጣኙን ዴቪድ ሞይስ ዳግም ከመለሰ በኋላ በጥሩ መነቃቃት ላይ ነው።
በኤቨርተን ሜዳ ጉዲሰን ፓርክ የሚደረገው ጨዋታ ለአርሰናል ፈታኝ እንደሚኾን ይጠበቃል። በዋንጫ ፉክክር ውስጥ ያለው አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ በማሸነፍ ከሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ይፋለማል።
ከሜዳው ውጭ ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ ያለው አርሰናል በዛሬው ጨዋታ ድል ይቀናው ይኾን ? የሚለው ይጠበቃል። ጨዋታው ቀን 8: 30 ይጀምራል።
በፕሪሚየር ሊጉ ሌሎች ጨዋታዎችም ሲካሄዱ ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን፣ ኢፕስዊች ታውን ከዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከቦርንማውዝ በተመሳሳይ 11:00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አስቶን ቪላ ከኖቲንግሃም ፎረስት የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ምሽት 1: 30 ይጀመራል።
አስቶን ቪላ ከኖቲንግሃም ፎረስት የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!