በመንግሥት ሠራተኞች መካከል የሚካሄደው ስፓርታዊ ውድድር በፍኖተ ሰላም ከተማ ተጀመረ።

0
136

ፍኖተ ሰላም: መጋቢት 26/2017 ዓ.ም ( አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር በመንግሥት ሠራተኞች መካከል የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ወርቁ በላይ የስፖርት ውድድሩ ጤናን ከመጠበቅ ባለፈ የእርስ በርስ መስተጋብርን ከማዳበር አንጻርም አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል ።

የመንግሥት ሠራተኞችን በእንዲህ አይነት የስፓርት ውድድሮች ማሳተፍ ንቁ ሠራተኛ በመፍጠር በኩል አበርክቶው የጎላ መኾኑንም አንስተዋል ።

የመንግሥት ሠራተኞች የተቋማት የእርስ በርስ ውድድሩ በእጅ እና በእግር ኳስ ጨዋታዎች የሚከናወን መኾኑን የገለጹት ደግሞ የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቢኒያም ጌጡ ናቸው።

ውድድሩ በሥነ ልቦና እና በአካሉ የዳበረ ሠራተኛ ለመፍጠር አላማ ያደረገ ነውም ብለዋል። ውድድሩ በተለይም በአካባቢው የተቀዛቀዘውን የስፖርት ዘርፍ በማነቃቃት ሚናው የጎላ መኾኑንም ተናግረዋል።

በውድድር ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ኢትዮ ቴሌኮም ፍኖተ ሰላም ቅርንጫፍ እና ፍኖተ ሰላም ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎ የተጫወቱ ሲኾን ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት 3 ለ1 በኾነ ውጤት አሸንፏል።

የተጀመረው ስፓርታዊ ውድድር የሠራተኞችን የእርስ በርስ ግንኙነት እንደሚያዳብር እና ታዳጊ ስፖርተኞችን ከማነሳሳት አንጻርም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የውድድሩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

በአካባቢው ያለውን የስፖርት አቅም ለማነሳሳት እንደሚረዳም ገልጸዋል ተወዳዳሪዎቹ።

ውድድሩ ለአንድ ወር ያህል እንደሚዘልቅም ተገልጿል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here