ኬቬን ዲብሮይና ከሲቲ ጋር ለመለያየት ወሰነ።

0
112

ባሕር ዳር: መጋቢት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ሲቲ በቅርብ ጊዚያት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን የበላይነት ወስዷል። ለክለቡ ስኬታማነት በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል ደግሞ አማካዩ ዲብሮይና ግንባር ቀደሙ ነው። ተጫዋቹ በ2015 ከጀርመኑ ወልፍስበርግ ነበር ማንቸስተር ሲቲን የተቀላቀለው።

በክለቡ በቆየባቸው 10 ዓመታትም ስድስት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና አንድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል። ሁለት የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ እና አምስት የካራቦ ዋንጫንም ከክለቡ ጋር አሳክቷል።

ይህን ሁሉ ክብር የአሳካበት ሲቲን በዓመቱ መጨረሻ እንደሚለቅ ዲብሮይና በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አሳውቋል።

በተመሳሳይ ክርስቲያን ኤሪክሰን በዚህ ውድድር መጨረሻ ኦልድትራፎርድን እንደሚለቅ አረጋግጧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here