የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሲቀጥል የለንደን ደርቢ ይጠበቃል።

0
99

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት ቼልሲ ቶትንሃምን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ያስተናግዳል። ሁለቱ ቡድኖች ያሉበትን ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርጉት ትንቅንቅ ትኩረት የሚስብ እንደሚኾን ይጠበቃል።

ቼልሲ በፕሪምየር ሊጉ ስድስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲኾን 49 ነጥቦችን ሠብሥቧል። ቶትንሃም ደግሞ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 34 ነጥቦችንም ሠብሥቧል። ቼልሲ በአጠቃላይ 53 ጎሎችን ሲያስቆጥር 37 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ቶትንሃም በበኩሉ 55 ጎሎችን ሲያስቆጥር 43 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

ቼልሲ ከቶትንሃም ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች የተሻለ ሪከርድ አለው። እስካኹን 162 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን 73 ጊዜ ቼልሲ፣ ቶትንሃም ደግሞ 50 ጊዜ አሸንፈዋል። 39 ጊዜ ነጥብ ተጋርተዋል። ይህ የለንደን ደርቢ ጨዋታ የሚካሄደው ምሽት 4:00 ሰዓት ነው።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here