ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገራት ጨዋታ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሊግ ጨዋታ ተመልሷል። በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ 30ኛ ሣምንት ዛሬ ምሽት ሦስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
በለንደን ደርቢ አርሰናልን ከፉልሃም ያገናኘው ጨዋታ በአርሰናል 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል። የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ሚኬል ሜሪኖ እና ከጉዳት የተመለሰው ቡካዮ ሰካ አስቆጥረዋል።
በደርቢው ጨዋታ ድል የቀናው አርሰናል ከሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ዘጠኝ አጥብቧል። አርሰናል 61 ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሊቨርፑል በ70 ነጥብ በመሰብሰብ ሊጉን እየመራ ነው።
በሜዳው እና በደጋፊው በፊት ማንቸስተር ዩናይትድን የጋበዘው ኖቲንግሃም ፎረስት 1 ለ 0 አሸንፏል። የኖቲንግሃም ፎረስትን የማሸነፊያ ግብ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች አንቶኒ ኢላንጋ አስቆጥሯል።
የውድድር ዓመቱ ክስተት የኾነው ኖቲንግሃም ፎረስት 57 ነጥብ በመሰብሰብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሌላ ጨዋታ ዎልቨርሃምፕተን ደግሞ ዌስትሃምን 1ለ0 አሸንፏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!