አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ዛሬ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር ተጠባቂ ጨዋታዎችን ያደርጋሉ።

0
165

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል እና ፉልሃም የሚፋለሙበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ይህ ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች ወሳኝ ሲሆን በተለይም አርሰናል በሜዳው የሚያደርገው በመኾኑ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል።

የአርሰናል ክንፍ ተጨዋቹ ቡካዮ ሳካ ከሦስት ወራት የጉዳት ጊዜ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ዝግጁ መኾኑ ለአርሰናል ደጋፊዎች ትልቅ ብስራት ነው። ጁርየን ቲምበርም ከህመሙ አገግሞ ወደ ሥብሥቡ ተመልሷል። ኾኖም ሪካርዶ ካላፊዮሪ በጉልበት ጉዳት ምክንያት ለተወሰኑ ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።

በፉልሃም በኩል አሠልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ካደረጉት የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ በኋላ ቡድናቸው ከትንሽ ድካም እና ጉዳት በስተቀር ምንም አይነት ችግር እንደሌለበት ተናግረዋል። ነገር ግን የቀድሞው የአርሰናል ተጨዋች ሪስ ኔልሰን በደረሰበት የጡንቻ ጉዳት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ላይሰለፉ ከሚችሉ ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ተነግሯል።

አርሰናል በሜዳው ከፉልሃም ጋር ያደረጋቸውን 31 የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፎ አያውቅም። ይህ በእንግሊዝ ሊግ ታሪክ አንድ ቡድን በሌላ ቡድን ሳይሸነፍ ብዙ በሜዳው ጨዋታዎችን ያደረገበት ሪከርድ ነው። ሚኬል አርቴታ የሚመራው ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን በለንደን ደርቢ ከማንኛውም ቡድን የበለጠ 20 ነጥብ አስመዝግቧል።

ፉልሃም በበኩሉ ሦስት ተከታታይ ጨዋታወችን ከሜዳው ውጭ ድሎችን ሲያስመዘግብ ይህ ግስጋሴ በብራይተን ያለመሸነፍ ጉዞው ተገትቷል። በዚህ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን 13 የፉልሃም ጎሎች በተቀያሪ ተጨዋቾች ተመዝግበዋል ይህም ከማንኛውም ቡድን የበለጠ ነው።

አንቶኒ ሮቢንሰን በፕሪሚየር ሊጉ 50 ኳሶችን ማስቆጠር ችሏል። ይህም ከሊቨርፑሉ ራያን ግራቨንበርች ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ጋር እኩል ሁኗል። በዚህ ጨዋታ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንደሚኖር ይጠበቃል። አርሰናል በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በማሸነፍ ያለውን ጉዞ አጠናክሮ መቀጠል ይፈልጋል።

ፉልሃም ደግሞ ከሜዳው ውጭ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ነው ዛሬ የሚጫወተው። ጨዋታውም ምሽት አራት ሰዓት ከ45 ይደረጋል።

ሌሎች የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎችም ሲቀጥሉ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ኖቲንግሀም ፎረስትን 5 ሰዓት ከ45 ሲገጥም በተመሳሳይ ሰዓት ወልቨስ እና ዌስትሀም የሚያደርጉት ሌላው የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here