አጫጭር ስፖርታዊ ወሬዎች፡፡

0
126

ባሕር ዳር: መጋቢት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

👉 የማንቸስተር ዩናይትዱ አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም ስለ ራሽፎርድ በአስቶን ቪላ ጥሩ አፈጻጸም ሲጠየቁ በሰጡት ምላሽ እኔ በቡድኔ ላይ ብቻ ነው የማተኩረው ራሽፎርድ በአሁኑ ሰዓት የእኔ ተጫዋች አይደለም። ነገር ግን ተጫዋቾቻችን በውሰት ላይ ኾነው ጥሩ ሲጫወቱ ደስተኛ ነኝ ብለዋል፡፡

👉 ካርሎ አንችሎቲ ሪያል ማድሪድ እግር ኳስን የሚጫወትበት መንገድ በጣም ደስ ይለኛል። አሁን ብቻ ሳይኾን ባለፉት ሦስት ዓመታትም ጭምር ብለዋል፡፡

👉 የአይደን ሄቨን ጉዳት ከባድ እንዳልኾነ እና በቅርቡ እንደሚመለስ ተረጋግጧል። ሩበን አሞሪም በሰጡት አስተያየት አይደን አሁን ዝግጁ አይደለም ግን በዚህ የውድድር ዘመን በእርግጠኝነት ይጫወታል ነው ያሉት፡፡

👉 ካርሎ አንችሎቲ ምኞቴ ኪሊያን ምባፔ በሪያል ማድሪድ የክርስቲያኖን ቁጥሮች እንዲተካ ነው፡፡ ይህ እንዲኾን የሚያስችል ብቃት አለው፡፡ ይህ እንዲኾን እመኛለሁ፤ ኪሊያን ምባፔ ይህን ማድረግ ይችላል ብለዋል፡፡

👉 ተር ስቴገን ዛሬ የባርሴሎናን ልምምድ ከቡድኑ ጋር በከፊል እያደረገ ነው፡፡ ተጫዋቹ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ላይ በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ውጭ ነበር። ነገር ግን ግብ ጠባቂው በዚህ ወሳኝ ወቅት ለቡድኑ መሰለፍ እና መርዳት ይፈለጋል ነው የተባለው።

👉 ሪካርዶ ካላፊዮሪ ጉዳት እንደደረሰበት እና ለሪያል ማድሪድ ጨዋታ ለመድረሱ አጠራጣሪ እንደኾነ አርቴታ ተናግሯል፡፡ ጉዳቱ የሚያሳዝን ቢኾንም የከፋ ጉዳት አለመድረሱ ግን ዕድለኛ ነው ተብሏል። በሳምንታት ውስጥ እንደሚድን ተስፋ እናደርጋለን ነው ያሉት፡፡

አርቴታ ቡካዮ ሳካ በዚህ ሳምንት ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አረጋግጧል፡፡ ቡካዮ ለመሰለፍ ዝግጁ ነው፡፡ ከፉልሃም ጋር ባለው ጨዋታ መሰለፍ ይችላል፤ ነገ እናየዋለን ነው ያሉት፡፡ ቡካዮ መጫወቱን በጣም ስለሚፈልገው እየገፋ ነው ሲል አርቴታ ገልጿል፡፡ ሳካ ከሪያል ማድሪድ ጋር ቡድኑ ለሚያደረገው ጨዋታ ብቁ እና ዝግጁ ይኾናል ነው የተባለው።

👉 ፔድሪ ስለ ባሎንዶር ማሸነፍ ሲጠየቅ በሰጠው መልስ ራፊንሃ ወይም ላሚን ባሎንዶርን ቢያሸንፉ እመርጣለሁ ብሏል፡፡ ፔድሪ እንዳላው ልዩነት የሚፈጥሩት እነሱ ናቸው፤ ቡድኑ ዋንጫዎችን እስካሸነፈ ድረስ ደስተኛ ነኝ ሲል ለቲቪ ሦስት ተናግሯል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here