ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ወደ ሪያል ማድሪድ ሊያቀና ነው ተብሏል። የሊቨርፑሉ እንግሊዛዊ ተከላካይ አርኖልድ በአምስት ዓመት ውል ከሪያል ማድሪድ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። ሰኔ ላይም ሪያል ማድሪድን እንደሚቀላቀል ታውቋል።
ሪያልማድሪድ በተመሳሳይ ኒኮ ዊሊያምስን ለማስፈረም እየተከታተለው ነው። ሪያል ማድሪድ የ22 ዓመቱን የአትሌቲክ ቢልባኦ እና የስፔን ክንፍ ተጫዋች ኒኮ ዊሊያምስን ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው።
የብራዚሉ ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር ወደ ሳውዲ አረቢያ በከፍተኛ ገንዘብ የሚዛወር ከኾነ በሚል ነው ማድሪድ ኒኮን ተተኪ ለማድረግ እየሠራ ያለው።
ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ተመለከተው መረጃ ስናልፍ 10 ተጫዋቾች ከክለብ ይወጣሉ ተብሏል። ዩናይትድ ተጫዋቾችን የሚያስወጣው አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ነው።
ባርሴሎና የ24 ዓመቱን የኒውካስትል እና የጣሊያን አማካይ ሳንድሮ ቶናሊን እንዲኹም ስዊድናዊን አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳክን ለማግኘት ጥረት ላይ መኾኑ ተነግሯል።
እንግሊዛዊው ተከላካይ ጃራድ ብራንትዋይት በማንቸስተር ዩናይትድ እና በሊቨርፑል መፈለጉን ተከትሎ በኤቨርተን ያለውን የወደፊት ዕጣ ፈንታ እያሰበ መኾኑን ቢቢሲ አገኘውት ባለው ጭምጭምታ ገልጿል።
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!