ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ ሴራሊዮን ከጊኒቢሳው ዛሬ ይጫወታሉ። በዚህ ምድብ አራት ጨዋታዎችን በማካሄድ በ10 ነጥብ ምድቡን እየመራች ነው። ስድስት ነጥብ ያላት ጊኒቢሳው ሁለተኛ ናት። ሴራሊዮን አምስት ነጥብ አላት።
ከምድቡ ለማለፍ ከፍተኛ ፉክክር እየተካሄደበት ባለው በዚህ ምድብ ዛሬ አሸንፎ ሦስት ነጥብ ለማግኘት ከፍተኛ ፉክክር ነው የሚካሄደው።
ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችም ዛሬ ይካሄዳሉ። ዚምባብዌ ከቤኒን፣ ኬፕቨርዴ ከሞሪሸስ፣ ሊቢያ ከአንጎላ፣ ጋቦን ከሲሸልስ፣ ጋምቢያ ከኬንያ፣ ሞዛምቢክ ከኡጋንዳ፣ ማላዊ ከናሚቢያ እና ኮሞሮስ ከማሊ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!