ባሕር ዳር: መጋቢት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በቅርቡ የዋልያዎቹ አሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ ሲያደርጉ ጥሪ የተደረገለት እና ለደቡብ አፍሪካው ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እየተጫወተ የሚገኘው አቡበከር ናስር ዛሬ ረፋድ ብሔራዊ ቡድኑን በአዲስ አበባ ስታዲየም የልምምድ ስፍራ ላይ ተቀላቅሏል።
አቡበከር ለብሔራዊ ቡድኑ ለመጨረሻ ጊዜ አገልግሎት የሰጠው ሰኔ 02/2014 ዓ.ም ከግብጽ ጋር በተደረገው ጨዋታ ነበር።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!