ኢትዮጵያ መድን መሪነቱን አጠናከረ።

0
94

ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ22ኛ ሳምንት የኢዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቶታል።

የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።

ለኢትዮጵያ መድን ግቦቹን በ36’ኛው ደቂቃ ኪቲካ ጅማ እና በ49ኛው ደቂቃ አቡበከር ሳኒ አስቆጥረዋል።

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ ከመሸነፍ ያልዳነባትን ግብ በ9ኛው ደቂቃ አለን ካይዋ ማስቆጠር ችሏል።

የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን ነጥቡን 41 በማድረስ መሪነቱን አጠናክሯል።
22ኛ ሳምንት የኢዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ 12:00 ሰዓት ሲቀጥል ወላይታ ድቻ ከውልዋሎ አዲግራት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here