ምሽቱ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደምቃል።

0
120

ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ምሽት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ሲደረጉ ምሽት 5:00 ላይ በአንፊልድ ሮድ ስታዲዮም ሊቨርፑልን ከፒኤስጂ የሚያገናኘው ጨዋታ ይጠበቃል። ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በሁሉም ውድድር ባደረጓቸው ያለፉት አምስት የእርስ በርስ ግንኙነቶች ሊቨርፑል ሦስቱን ጨዋታ በማሸነፍ ቀዳሚ ነው። ፒኤስጂ በሁለቱ ጨዋታ ድል ቀንቶት ነበር።

በመጀመሪያ ዙር 16ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሊቨርፑል ወደ ፈረንሳይ አቅንቶ ሀርቪ ኤሊዮት ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1ለ0 በኾነ ውጤት አሸንፎ መመለሱ ይታወሳል። የሁለቱ ቡድኖች የድምር ውጤት አሸናፊ በሩብ ፍጻሜው ከአስቶንቪላ እና ከክለብ ብሩዥ አሸናፊ ጋር ይገናኛል።

ይህ ተጠበቂ ጨዋታ በአሚኮ ራዲዮ ጣቢያዎች በቀጥታ ለእግር ኳስ አፍቃሪያን ይደረሳል። በተመሳሳይ ምሽት 5:00 ላይ በሚደረግ በሌላ ጨዋታ ሁለቱ የጀርመን ክለቦች ባየር ሊቨርኩሰን እና ባየርን ሙኒክ በባየርን አሬና ወደ ሩብ ፍጻሜው ለመግባት ይፋለማሉ።

የሁለቱ ቡድን የድምር ውጤት አሸናፊ ከኢንተር ሚላን እና ፌይኖርድ አሸናፊ ጋር በሩብ ፍጻሜው ይፋለማል። የጣሊያኑ ክለብ ኢንተርሚላን በሜዳው ጁሴፔ ሜዛ ምሽት 5:00 ላይ የኔዘርላንዱን ክለብ ፌይኖርድን ያስተናግዳል።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ኢንተርሚላን ወደ ኔዘርላንድስ አቅንቶ በማርከስ ቱራም እና ላውታሮ ማርቲኔዝ ግቦች 2 ለ 0 በኾነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል። ከነዚህ ጨዋታዎች ቀደም ብሎ ምሽት 2:45 ላይ ባርሴሎና በሜዳው ቤኔፊካን ያስተናግዳል።

በመጀመሪያው ዙር የእርስ በርስ ግንኙነት የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ በራፊኒሃ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here