የዝውውር ዜና

0
393

ባሕር ዳር: ጥር 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ24 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊው የባየርሙኒክ ተከላካይ ማቲጂስ ደሊጊት በቀያይ ሰይጣኖቹ ማንቸስተር ዩናይትዶች በእጅጉ እየተፈለገ ነው፡፡
ፉልሃም የ22 ዓመቱን የፍሉሚንሴ አማካኝ አንድሬን ለማስፈረም 30 ሚሊዮን ፓውንድ አቅርቧል፡፡

ዌስትሃም የማንቸስተር ሲቲውን አማካይ ካልቪን ፊሊፕስን ለማስፈረም ከሚፈልጉ ክለቦች አንዱ ኾኗል፡፡

ማንቸስተር ሲቲ የ24 ዓመቱን የቶትንሀም የቀኝ መስመር ተከላካይ ፔድሮ ፖሮ እና የአስቶንቪላው አማካኝ ዳግላስ ሉዊዝን ወደ ክለቡ ለመመለስ 200 ሚሊዮን ፓውንድ ለማውጣት ከፍተኛ ፍላጎቱን እንዳሳየ ዘ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለቦች የሊቨርፑሉን የ31 ዓመት ግብፃዊ ሙሐመድ ሳላህን ለማስፈረም እየተሯሯጡ ነው ሲል ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል፡፡

ኒውካስል ብራዚላዊውን የ27 ዓመቱን አማካኝ ጆሊንተንን “ሊሸጥ” የሚችለው የኮንትራት ውሉ ሲገባደድ እንደኾነ አስታውቋል፡፡

አስቶንቪላ የሚድልስቦሮውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ሞርጋን ሮጀርስን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ሊድስ ዩናይትድ የቶተንሃሙን ተከላካይ ጆ ሮዶን ለማስፈረም 15 ሚሊዮን ፓውንድ ማቅረቡን ዘ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here