ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድል ቀንቶታል።

0
111

ባሕር ዳር: የካቲት 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ዛሬ ሲጀመር 12:00 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ስሑል ሽሬ ተገናኝተው ነበር። በዚህ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስሑል ሽሬን 1ለ0 በማሸነፍ ሦስት ነጥቡን አሳክቷል።

የማሸነፊያ ግቧንም በ42ኛው ደቂቃ ያሬድ የማነ አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ28 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ሲቀመጥ ስሑል ሽሬ በ15 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ስጋት ውስጥ በ17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሠንጠረዡን ኢትዮጵያ መድን በ38 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና በ33 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሀድያ ሆሳዕና ደግሞ በ32 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here