ባሕር ዳር: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በኾነ አቻ ውጤት አጠናቅቋል።
የቀያዮቹ ሴጣኖቹን ግብ ጆሽዋ ዚርኪዜ ሲያስቆጥር ኦያርዛባል ሪያል ሶሴዳድን አቻ አድርጓል።
ቼልሲ ከኮቤንሀቨን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 2 ለ 1 በኾነ ውጤት አሸንፈዋል።
የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ሬስ ጄምስ እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ ማስቆጠር ችለዋል።
ቶተንሀም በበኩሉ ከአልክማር ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ 1 ለ 0 በኾነ ውጤት ተሸንፏል።
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ውድድር መድረኮች ምንም ጨዋታ ያልተሸነፉ ቡድኖች ኾነው ቀጥለዋል።
በሌሎች የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ሬንጀርስ ፌነርባቼን 3 ለ 1 ሲረታ ኦሎምፒክ ሊዮን ከ ኤፍ ሲ ኤስ ቢ ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 1 አሸንፏል።
በታዘብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!