በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ሪያል ማድሪድ እና አርሰናል አሸነፉ።

0
303

ባሕር ዳር: የካቲት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሪያል ማድሪድ እና አርሰናል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

ሪያል ማድሪድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ያደረገውን የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ በሮድሪጎ እና ብራሂም ዲያዝ ግቦች 2 ለ 1 በኾነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የአትሌቲኮ ማድሪድን ብቸኛ ግብ ጁሊየን አልቫሬዝ አስቆጥሯል።

አርሰናል ከሜዳው ውጪ ከኔዘርላንዱ ክለብ ፒኤስቪ ጋር ያደረገውን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 7 ለ 1 በኾነ ሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ኦዴጋርድ ሁለት፣ ጁሪየን ቲምበር፣ ንዋኔሪ፣ ሜሪኖ፣ ካላፊዮሪ እና ትሮሳርድ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በሌላ ጨዋታ ቦርስያ ዶርትመንድ ከሊል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በኾነ አቻ ውጤት አጠናቅቀዋል።

በታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here