ደማቁ ጨዋታ በጣና ሞገዶቹ እና በፈረሰኞቹ መካከል ይጠበቃል።

0
136

ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ የጣና ሞገዶቹ እና የፈረሰኞቹ ፍልሚያ ይጠበቃል። የጣና ሞገዶቹ በፕሪምየርሊጉ ወጥ አቋም እያሳዩ ባይኾንም ባለፉት ጨዋታዎች የተሻለ ሥነልቦና እንደገነቡ ታይቷል።

ሥብሥቡ በ26 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲኾን ባለፉት ያደረጓቸውን አምስት ያክል ጨዋታዎችን በማንሳት ያላቸውን ወቅታዊ አቋም ስንፈትሽ በኢትዮጵያ ቡና 2ለ1 እና በኢትዮጵያ መድን 1ለ0 ተሸንፈዋል። ከመቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ደግሞ አንድ አቻ ነው የተጠናቀቀው።

አጼዎቹን 2ለ1 እና ሀዋሳ ከተማን 1ለ0 በማሸነፍ ባለፉት ጊዜያት ወጥ ያልኾነ አቋም ግን ደግሞ ጥሩ የማሸነፍ ሥነልቦና በቅርብ እንደገነቡ ያሳያል። ተጋጣሚያቸው ጊዮርጊሶች ደግሞ በ29 ነጥብ በፕሪምየርሊጉ የተሻለ ደረጃ ይዘው ተቀምጠዋል። ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ላይ የነበራቸው አቋም ሲታይ በሀድያ ሆሳህናን 1ለ0 ሲሸነፉ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለግብ እና ከሀዋሳ ከተማ ጋር 1ለ1 ተለያይተዋል።

ወላይታ ድቻን እና ድሬዳዋ ከተማን በተመሳሳይ 2ለ0 በኾነ ውጤት ማሸነፍ የቻለ ሥብሥብ ነው። ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በፊት 12 ጊዜ ተናነኝተዋል። ሦስት ጊዜ በሁለቱም በኩል ሲሸናነፉ ስድስት ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። በሌላ የ20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ 9 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ እና መቻል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here