ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቶኪዮ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል። በወንዶች ታደሰ ታከለ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ አትሌት ሱቱሜ አሰፋ አሸንፋለች።
በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው በዚህ ማራቶን በሴቶች አትሌት ሱቱሜ አሰፋ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ31ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።
በወንዶች ደግሞ አትሌት ታደሰ ታከለ በ2 ሰዓት ከ3 ደቂቃ 23 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቱን ጭምር በማሻሻል አሸንፏል።
አትሌት ደረሳ ገለታም ሁለተኛ ደረጃ ይዞ እንዳጠናቀቀ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!